ዉድ አንባብያን ለስጋዊው ጤንነታችሁ እና ለመንፈሳዊው ሕይወታችሁ እንደምን አላችሁልን? ዛሬ በይፈለጋል ርዕሳችን ብቅ ብለናልና ምንድነው የሚፈለገው? ብላችሁ ታስቡ ወይም ትጠይቁ ይሆናል፡፡
እንግዲህ በዚህ ተኩላ በበዛበትና የበግ ለምድ ለብሰው በበጎች መካከል ሰርገው የገቡ ነጣቂዎች ማቴ 7÷15 መድረክ ይዘው ቤተክርስቲያናችንን ለመውረስ በተዘጋጁበት ሰዓት @ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አባቶች እና መምህራን እየተሰደዱ ከስራ እተባረሩ በሚገኙበት በዚህ ወቅት @ የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ተጥሶ የግለሰቦች ዉሳኔና ጥቅም ብቻ እየተከበረ በሚገኝበት@ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ ያልሆኑ የሌላ እምነት ተከታዮች በቤተክርስቲያኒቱ መድረክ ባለቤት በሆኑበት@ ብፁአን አባቶች ከሀ/ስብከታቸው በተሰደዱበት በዚህ ዘመን@ የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ተቀይሮ የሌላ ድምË በምንሰማበት@ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ያስፈልጋታል በሚባልበት@ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ነገረ ቅዱሳን ስለ Ìም ስለ ስግደት ማስተማር ለሕይወት የማይጠቅም እርባና የለሽ እንደሆነ በሚያስወሩበት@ ቤተ ክርስቲያንን ያረጀች ያፈጀች "አሮጊተý ሣራ' አድርገው በሚያስተምሩበት@ በሃይማኖት ከማይመስሉአችሁ ጋር አንድ ካልሆናችሁ ብፁዕ አትባሉም ተብለን በምንሰበክበት እና የመሳሰሉት ፍፁም የቤተ ክርስቲያናችን ዶግማዋ@ ስርዓተýና ትውፊተý እየተጣሰ በሚገኝበት በዚህ ወቅት እነኚህን የበግ ለምድ ለብሰው በበጎች መካከል የገቡትን አጋልጦ የሚያስወጣ ለቤተ ክርስቲያኑ የሚቆም ትውልድ ይፈለጋል፡፡
እስከ ዛሬ የተዋሕዶ ልጆች ስለ አባቶቻችን የእምነት ተጋድሎ ስናወራ ኖረናል፡፡ ዛሬ ግን ከማውራት ያለፈ ስራን እንድንሰራ እግዚአብሔር ይፈልገናል፡፡ አሁን እውን ክርስቲያን መሆን አለመሆናችን የሚፈተንበት ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡ የአባቶቹን ታሪክ ሲያወራ የነበረውን የሚተገብር ሰው ይፈለጋል፡፡ ዕብ 13÷7 "የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩአችሁን መምህራኖቻችሁን ዐስቡ; መልካም ጠባያቸውን አይታችሁ በእምነት ምሰሉአቸው፡፡ ' እንደተባለው ይህንን ቃል የሚተገብር ሰው ይፈለጋል፡፡ እንዲሁም ዕብ 11÷36 "... የገረፉኣቸው@ የዘበቱባቸውና ያሰሩአቸው ወደ ወህኒ ያገቡአቸው አሉ፡፡ በመጋዝ የሰነጠቁአቸው@ በድንጋይ የወገሩአቸው@ በሰይፍም ስለት የገደሉአቸው አሉ … መከራ ተቀበሉ … ' ይህንን መከራ ተቀብለው አባቶች የሰጡን ቅድስት እምነት ግን ዛሬ በኛ ዘመን ተደፈረች ታዲያ የዚህ ዘመን ሰው ከወሬ ያለፈ ሥራ እንዲሰራ ይፈለጋል፡፡ ስለዚህ የታሪክና የትውልድ ተወቃሽ ላለመሆን ወገኔ ተነስ@ ተነሺ … የሰማህ ላልሰማ አሰማ ብፁአን አባቶቻችንን ለማገዝና ዶግማዋ@ ስርዓተýና ትውፊተý የተጠበቀች ቤተ ክርስቲያን ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ለግንቦቱ ሲኖዶስ አዲስ አበባ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንገናኝ፡፡ ጥያቄያችን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ነው!!!
No comments:
Post a Comment