የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎቷን በመፈጸም ያሳለፈቻቸው ዘመናት ሁሉ እንዲሁ አልጋ በአልጋ የሆነ አልነበረም። እንደየጊዜው ሁኔታ እንደ ፈተናው መጠንና ጠባይ የተለያዩ ፈተናዎችን በአባቶቻችን ተጋድሎና ፅናት አልፋ ዛሬ ለእኛ ደርሳለች።
በየዘመናቱ የገጠሟት ፈተናዎች የዩዲት ጉዲት መነሳት ፣ የግራኝ አህመድ ወረራ ፣ የካቶሊክ ሚሲዮናዊያን እንቅስቃሴ፣ የቅባትና የጸጋ እሾህ ፣ ዘመነ መሳፍንት እና የመሳሰሉት ቤ/ክንን ከገጠሟት ታላላቅ ፈተናዎች ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።
በተለይ በታሪክ እንደምንረዳው ለአፍሪካዊያን ክርስትና እንግዳ ያልነበረና አፍሪካዊያንም ለክርስትና ከዕለተ አርብ ከቀራንዮ ጀምሮ ሱታፌ ያላቸው መሆኑን ብንረዳም ዛሬ ግን ስንት ሊቃውንትንና ቅዱሳንን ያፈሩት የአፍሪካ ክፍሎች ዛሬ ዝክራቸው ጠፍቷል። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ግን በተሻለ ሁኔታ ዘመናትን ለመዝለቅና ከዛሬ ለመድረስ ችሏል። ሆናም ግን የኢትዮጵያ ቤ/ክ እንደሌሎቹ ሀገራት ታሪክ ሆና አለመቅረቷ ወይም ደግሞ በምዕራባዊያኑ ሚሲዮናውያን የተመሰረተችና ከእነርሱ ፍላጎት አንጻር የተቃኘች አለመሆኗ ብዙዎችን አያስደስታቸውም። ከዚህም የተነሳ በተለየ ስልትና ዘዴ ቤ/ክን “ተሐድሶ ያስፈልጋታል” በሚል ሽፋን ዶግማዋን ፣ ቀኖናዋንና ሥርዓቷን በአጠቃላይ እርሷነቷን የመለወጥና ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ ደፋ ቀና በማለት ላይ ይገኛሉ።
ይህንን ዓላማም ተግባራዊ ለማድረግ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ያልሆኑ ግን ኦርቶዶክስ ነን በማለት ሰርገው ገብተው በቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደር መስመሮች ላይ የተቀመጡ ግለሰቦችን በግልፅ ማየት ተጀምሯል። ይህም ሲደረግ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪ የሆኑትን ቅዱስ ፓትርያሪክ መከታና አጋዥ በማድረግ የመንቀሳቀሳቸው ምስጢር ይኽው ነው። ለዚህም በቅርቡ በሐዋሳ (በሲዳማ ፣ በጌዴዎ ፣ አማሮና ቡርጂ) ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅነት የተሾሙት ግለሰብ አንድ ማሳያ ናቸው ። ፓትርያሪኩ በተደጋጋሚ በሐዋሳ ጉዳይ ላይ የሚያራምዱትስ ሃሳብ እውነት የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር ለመፍታት ወይስ ዓላማቸው ቤተ ክርስቲያን ዉስጧ ሰርጎ በመግባት ልጆቿን እስከ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኗ እንረክባለን ከሚሉት ጋር? የቋሚ ሲኖዶሱንም ሆነ የቅዱስ ሲኖዶሱን ወሳኔ ከአባቶቻችን ጋር በመሆን መንፈስ ቅዱስና እኛ ወስነናል ብለው የሚያምኑትን ውሳኔ ተግባራዊ እንዳያደርጉ ያስቸገራቸው ጉዳይ የማን ይበልጣል ብለው ይሆን? ይባስ ብሎ ቀድመን ለመጥቀስ እንደሞከርነው ሐዋሳ ላይ በስራ አስኪያጅነት የተሾሙት ግለሰብስ ቋሚ ሲኖዶስ ሳያምንበታና ሳይወስን መላክዎ አባታችን የማንን ጉዳይ እያስፈጸሙ ይሆን? ለማንኛውም ግለሰቡ ማንና ምን ስራ እየሰሩ እንዳሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳወቁ ግድ ይለናል።
በሕገ መንግስታዊው ስርዓታችን አንድ ዜጋ የፈለገውን እምነት የመከተል መብቱ የተረጋገጠ ነው። ሆኖም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስምና ሽፋን በውስጧ ሆኖ እምነቷን ፣ ሥርዓትና ትውፊቷን መጣስ እንዲሁም ከመመሪያ ውጭ መንፈሳዊ አገልግሎቷን ማወክ ፣ ምእመናኗን እያሳሰቱ ማሰኮብለል ሕጋዊ ተግባር እንዳልሆነ ሁሉም የሚገነዘበው ጉዳይ ነው።
ስለዚህ አሁን የምናነሳው ሰው ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የገቡ ግን የሌላ እምነት ተከታይ የሆኑ በቅርቡ በቅ/ፓትርያሪኩ በሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት የተሾሙ ግለሰብ ናቸው። በዚህ ግለሰብ ላይ የተገኙትን መረጃዎች ስናቀርብ ግለሰቡ
1. የመካነ ኢየሱስ እምነት ድርጅት አባል መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በራሳቸው እጅ የተጻፈ ደብዳቤ
2. የቅን ልቦና መንፈሳዊና የፈውስ አገልግሎት የሚባል የእምነት ተቋም በፍትሕ ሚኒስቴር ፍቃድ አውጥተው ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸው
3. በተራ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰውን የእምነት ድርጅት በመመስረት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን መንፈሳዊ አገልግሎት የሚያውክ ሥራ ሲሰሩ መቆየታቸው
4. የተሐድሶን ስራ በስፋት በቤተ ክርስቲያን ስር እየሰሩ ስለመቆየታቸው ለሌላኛው በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ስር ለሚገኝ አጋራቸው የጻፉትን የግል ደብዳቤ እና የመሳሰሉት ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን።
ውድ የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንግዲህ ምን እንጠብቅ ይሆን? አሁን መነሳት ለቤተ ክርሲቲያን መድረስ ያለብን ጊዜው አይደለም ትላላችሁ? ጉዳዩስ የሐዋሳ ምእመናን ችግር ብቻ ነው ብለን እናስብ ይሆን? ስለዚህ ያልሰማን በማሰማት ኃላፊነትን ወስደን ጉዳዩ ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን ልጅ የሚነካ ነውና ትላንት የሕንድ ቤተ ክርስቲያንን የከፈሉ ሰዎች ዛሬ የአኛንም ከፍለው ሳይወስዱ እንነሳ ለዚህ ሁሉ መሪ የሆኑትን እና የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ እየተጋፉ ለመናፍቃን በር የከፈቱትን ፓትርያሪክም በቃዎት ልንል ይገባል።
ስለዚህ ለግንቦቱ ሲኖዶስ አዲስ አበባ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ብንገናኝስ?.........................................
እግዚአብሔር ይርዳን በእለቱ እንገናኝ
ReplyDeleteE/R bete christianachinin yitebikilin! kidusan, asteway, behayimanot yetsenu ewinetegna abatoch E/R amilak ayasatan!!! lenanite degmo E/R amilak masitewalun tsegawin yabizalachihu!
ReplyDeleteageliglotachihun yibarkilachihu!
from hawassa university main capas
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በመናፍቃን ስትመራ ሆሆሆ…….. አይ አቡነ ጳውሎሰ
ReplyDeleteእግዚአብሔር ቤቱን ማጥሪያው ሰዓት ደረሰ መሰል፣
እነ አቡነ ጳውሎስ እየሰሩ ያሉት የውስጥ ደባ እየተጋለጠ መጣ ቀስበቀስ እንቁላል በእግር…… እንደተባለው ሁሉ በጥቂት ተስፈኞች በገንዘብ ተገዝተው ያለእምነታቸው ቤተክርስቲያናችንላይ፣ ቤተክርስቲያን አገልጋይ አባቶች ላይ እና እንዲሁም በምእመኑላይ ድንጋይ ሚወረውሩና ቖሻሻ የሚያቃጥሉ ቕጥረኛ ተሃድሶችን ወይም ወራሪዎች ለነርሱ ቤንጋዚን መስላ የታየቻቸውን ሐዋሳን ከመቆጣጠራቸው በፊት ይህን አነት ወረራ በቃ ልንላቸው ይገባናል፡፡ አቡነ ጳውሎስ ከግራኝ መሃመድ እንዴት አድርጌ ልለዮት ተግባሮት እኮ ተምሳሳይ ሆነ ከሐዋሳ ነውየመጣነው ብለው በጥቂት የእርሶ ጠበቆችና አሁን አዋሳን መራለሁ ብሎ በቅዠት የመጣው ግለስብ ጭምር ተደራጅተው ለመጡ ቦዘኔዎችና ህጻናት ብር ሰጥተው ስለ ምን ቤተክርስቲያን ላይ ድንጋይ ያስወረውራሉ
‹‹ ቅዱስ ሲኖዶስስ ይህን የቤተክርስቲያንን ክብር የሚነካ ተግባር ሲፈጸም እያየ ዝም ማለቱ ስለምንይሆን ዳሩ ከማን ይማሩ ››
ወገን ስለቤተክርስቲያናችን መታገል ካለብን ሰዓቱ ዓሁንና ዓሁን ብቻ ነው ምክኒያቱም ችግሩ የሐዋሳ ብቻ አይደለምና
ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ በእለቱ በመገኘት ስለ ቤተክርስትያናችን ልንታገል ይገባናል፡፡
ወላዲተ አምላክ ከልጃጋር ቤተክርስቲናችንን ትጠብቅልን፤፤
ብርሐነ ስላሴ ከሐዋሳ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
ReplyDeleteውድ ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ እንደምን አላችሁ ።
ከቅዱሳን ነብያት ከቅዱሳን ሐዋርያት እንዲሁም ከቅዱሳን ሰማዕታትና
ፃድቃን አባቶች የተቀበልናትን እውነተኛይቱን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
እምነትን እንደ ህንድ ለመክፈል የተንሱብንን እንዲሁም ይህንን
ድርጊት በመደገፍ ግንባር ቀደም የሆኑትን አቡነ ጳውሎስን በመቃወም
ለግቦት ፲ /፪ሺ፫ ዓ ም የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በቦታው ተገኝተን ተቃውሞአችንን እንድንገልፅ
ፅኑ መልክታችን ነው።
ረድኤተ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን።
አሜን።
ብዙአየሁ
ከሐዋሳ